Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዩኤል 1:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እን​ግ​ዲህ ለራ​ሳ​ችን ምን እን​ሰ​ብ​ስብ? የእ​ን​ስ​ሳት ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቀሱ፤ ማሰ​ማ​ሪያ የላ​ቸ​ው​ምና፥ የበ​ጎች መን​ጋ​ዎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 መንጎች እንደ ምን ጮኹ፣ ከብቶቹ ተደናግጠዋል፤ መሰማሪያ የላቸውምና፤ የበግ መንጎች እንኳ ተቸግረዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተቅበዘበዙ፥ የበግም መንጎች እየተሰቃዩ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የግጦሽ ሣር በማጣት ከብቶች ያላዝናሉ፤ የበጎች መንጋ ሳይቀሩ ተርበው በብርቱ ሥቃይ ላይ ይገኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተጠራጠሩ፥ የበግም መንጎች ጠፍተዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዩኤል 1:18
10 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ።


በሚ​ኖ​ሩ​ባት ሰዎች ክፋት ምድ​ሪቱ የም​ታ​ለ​ቅ​ሰ​ውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚ​ደ​ር​ቀው እስከ መቼ ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጻ​ሜ​ያ​ች​ንን አያ​ይም ብለ​ዋ​ልና እን​ስ​ሶ​ችና ወፎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋል።


እስ​ካ​ሁን ዓለም ሁሉ ያዘ​ነና የተ​ከዘ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።


ፈሳሹ ውኃ ደር​ቆ​አ​ልና፥ እሳ​ቱም የም​ድረ በዳ​ውን ውበት በል​ቶ​አ​ልና የም​ድር አራ​ዊት ወደ አንተ አን​ጋ​ጠጡ።


አክ​ዓ​ብም አብ​ድ​ዩን፥ “በሀ​ገሩ መካ​ከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እን​ሂድ፤ እን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ችን የም​ና​ድ​ን​በት ሣር ምና​ል​ባት እና​ገኝ እንደ ሆነ” አለው።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር በታ​ቦቷ ፊት ሆነው፥ ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይና​ገ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ የእ​ረ​ኞ​ችም ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ የቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም ራስ ይደ​ር​ቃል።”


ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥


ስለዚህ ሰማያት በላያችሁ ጠልን ከልክለዋል፥ ምድሪቱም ፍሬዋን ከልክላለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios