ኤርምያስ 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽና እድል ፈንታሽ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔን ረስተሽ፣ በከንቱ አማልክት ስለ ታመንሽ፣ ያወጅሁልሽ ድርሻሽ፣ ዕጣ ፈንታሽ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ፥ የለካሁልሽም ድርሻሽ ይህ ነው፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕድል ፈንታችሁም ይህ እንደሚሆን እግዚአብሔር ተናግሮአል። እርሱን ረስታችሁ በሐሰተኞች አማልክት ስለ ታመናችሁ በእናንተ ላይ ይህን ለማድረግ ወስኖአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ የለካሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እናንተም “ከሲኦል ጋር ተማምለናል፤ ከሞትም ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፤ ሐሰትንም መሸሸጊያን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና፥ ዐውሎ ነፋስም ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ትላላችሁና፥
እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፤ እጁም ከፈለችላቸው፤ ለዘለዓለም ይሰማሩባታል፤ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይወርሱአታል፤ በውስጥዋም ያርፉባታል።
በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፥ በኮረብቶችም ላይ ስለ አሽሟጠጡኝ ስለዚህ አስቀድመው የሠሩትን ሥራቸውን በብብታቸው እሰፍራለሁ።
ሰው ሁሉ ዕውቀት አጥቶ ሰንፎአል፤ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የለውምና።
ሕዝቤ ግን ረስተውኛል፤ ለከንቱ ነገርም አጥነዋል፤ የቀድሞውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማማውና ወደ ሰንከልካላው መንገድ ለመሄድ በመንገዳቸው ተሰናከሉ።
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን አድርገዋልና፤ የሕይወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተውኛል፥ የተነደሉትን ውኃውንም ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች ለራሳቸው ቈፍረዋል።
የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ዐምጸዋልና፥ ቅዱስ አምላካቸውንም ረስተዋልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእስራኤል ልጆች ልቅሶና ጩኸትም ተሰማ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዘንግተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ኀጢአትሽን ተሸከሚ።”
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
የእግዚአብሔርን እውነት ሐሰት አድርገዋታልና፤ ተዋርደውም ፍጥረቱን አምልከዋልና፤ ሁሉን የፈጠረውን ግን ተዉት፤ እርሱም ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ ነው፤ አሜን።