Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 34:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እር​ሱም ዕጣ ጣለ​ባ​ቸው፤ እጁም ከፈ​ለ​ች​ላ​ቸው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሰ​ማ​ሩ​ባ​ታል፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በው​ስ​ጥ​ዋም ያር​ፉ​ባ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤ እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች። ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፥ እጁም ለክታ ከፈለችላቸው፤ ለዘለዓለም የእነርሱ ትሆናለች፥ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይኖሩባታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር እያንዳንዳቸው የት መኖር እንደሚገባቸው ወሰነ፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለዘለዓለም ይኖሩበታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፥ እጁም በገመድ ከፈለችላቸው፥ ለዘላለም ይገዙአታል፥ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይቀመጡባታል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 34:17
11 Referencias Cruzadas  

ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏ​ፏቴ ውስጥ በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮ​ኻሉ፤ ያጠ​ፉ​ታ​ልም፤ እነ​ር​ሱም ከሩቅ ይወ​ር​ዳሉ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ዳለ እብቅ፥ በነ​ፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​ዞ​ረው እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር ትቢ​ያም ይበ​ተ​ናሉ።


በመ​ሸም ጊዜ ሳይ​ነጋ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ያን​ጊ​ዜም የይ​ሁዳ ወገ​ኖች “ይህ የወ​ራ​ሾች ርስት ነው፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​ንም ዕድል ፋንታ ይህ ነው” ይላሉ።


ጢሱም ወደ​ላይ ይወ​ጣል፤ ከት​ው​ልድ እስከ ትው​ል​ድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖ​ራ​ለች፤ ለብዙ ዘመ​ና​ትም ትጠ​ፋ​ለች።


ጭል​ፊ​ቶ​ችና ጃርት፥ ጕጕ​ትና ቍራም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም በመ​ፍ​ረስ ገመድ ይለ​ካሉ። አጋ​ን​ን​ትም ያድ​ሩ​ባ​ታል፤


ረስ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ታም​ነ​ሻ​ልና ዕጣ​ሽና እድል ፈን​ታሽ ይህ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰባ​ቱን የከ​ነ​ዓ​ንን አሕ​ዛብ አጥ​ፍቶ ምድ​ራ​ቸ​ውን አወ​ረ​ሳ​ቸው።


እር​ሱም በም​ድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖ​ሩ​ባ​ትም ዘንድ ዘመ​ን​ንና ቦታን ወስኖ ሠራ​ላ​ቸው።


ሕዝቡ ያዕ​ቆ​ብም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ገመድ ነው።


ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ኢያ​ሱም ምድ​ሩን ሊጽፉ የሄ​ዱ​ትን፥ “ሂዱ፤ ምድ​ሩ​ንም ዞራ​ችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመ​ለሱ፤ በዚ​ህም በሴሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos