“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መልካም ነገርም እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ አለቀሰ።
ኤርምያስ 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ታየኛለህ፤ ስለ አንተም ያለኝን ሐሳብ ትመረምራለህ። እንደሚታረዱ በጎች ንዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! አንተ ግን፥ አውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፥ ልቤንም ወደ አንተ መሆኑን ፈትነሃል፤ እንደ ሚታረድ በግ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ግን ታውቀኛለህ፤ ስለ አንተ ያለኝን አስተሳሰብ አይተህ ትፈትነኛለህ፤ እነዚህን ክፉ ሰዎች እንደሚታረዱ በጎች ውሰዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን፥ አቤቱ፥ አውቀኸኛል፥ አይተኸኛል፥ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፥ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው። |
“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መልካም ነገርም እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ አለቀሰ።
አምላኬ ሆይ፥ ልብን እንደምትመረምር፥ ጽድቅንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱ እንዳቀረበልህ በደስታ አይቻለሁ።
“ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ እስረኞችም ጩኸት እግዚአብሔር ይላል፥ አሁን እነሣለሁ፤ መድኀኒትን አደርጋለሁ፥ በእርሱም እገልጣለሁ።”
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤ ከሚያሳድዱኝም አድነኝ እንጂ፥ አትታገሣቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደቡኝ አስብ።
እኔም አንተን ተከትዬ አልደከምሁም፥ የሰውንም ቀን አልተመኘሁም፤ አንተ ታውቃለህ፤ ከከንፈሬ የወጣውም በፊትህ ነው።
አሳዳጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፤ በሁለት እጥፍ ጥፋት ቀጥቅጣቸው።
አቤቱ! ጽድቅን የምትፈትን ኵላሊትንና ልብን የምትመረምር የሠራዊት ጌታ ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ፍረድልኝ።
ሞዓብ ፈርሳለች፤ ከተሞቹዋም ጠፍተዋል፤ የተመረጡትም ጐልማሶችዋ ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ፍሬዋን ሁሉ አድርቁባት፤ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው ደርሳለችና፥ እነሱን የሚበቀሉበት ጊዜ ደርሷልና ወዮላቸው!
ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው።
እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤