Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 12:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ታየኛለህ፤ ስለ አንተም ያለኝን ሐሳብ ትመረምራለህ። እንደሚታረዱ በጎች ንዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አቤቱ! አንተ ግን፥ አውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፥ ልቤንም ወደ አንተ መሆኑን ፈትነሃል፤ እንደ ሚታረድ በግ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ግን ታውቀኛለህ፤ ስለ አንተ ያለኝን አስተሳሰብ አይተህ ትፈትነኛለህ፤ እነዚህን ክፉ ሰዎች እንደሚታረዱ በጎች ውሰዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አንተ ግን አቤቱ! ዐው​ቀ​ኸ​ኛል፤ አይ​ተ​ኸ​ኛል፤ ልቤ​ንም በፊ​ትህ ፈት​ነ​ሃል፤ እንደ በጎች ለመ​ታ​ረድ ጐት​ተህ ለያ​ቸው፤ ለመ​ታ​ረ​ድም ቀን አዘ​ጋ​ጃ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አንተ ግን፥ አቤቱ፥ አውቀኸኛል፥ አይተኸኛል፥ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፥ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 12:3
23 Referencias Cruzadas  

“እግዚአብሔር ሆይ፤ በፊትህ በታማኝነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፣ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ዐስብ፤” ሕዝቅያስም አምርሮ አለቀሰ።


አምላኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃድና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።


ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።


እግዚአብሔር ጻድቁንና ክፉውን ይመረምራል፤ ዐመፃን የሚወድዱትን ግን፣ ነፍሱ ትጠላቸዋለች።


እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤


ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋ ብለህ ፈተንኸኝ፤ ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤ አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣ አንተው ፍረድልኝ። ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ።


ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና።


እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ፤ እንግዲህ ዐስበኝ፤ ጐብኘኝም፤ አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ። ታጋሽ እንደ መሆንህ አታጥፋኝ፤ ባንተ ምክንያት የሚደርስብኝን ነቀፋ ዐስብ።


እረኛ ሆኜ አንተን ከማገልገል ወደ ኋላ አላልሁም፤ ክፉ ቀን እንዳልተመኘሁ ታውቃለህ፤ ከአንደበቴ የሚወጣውም በፊትህ ግልጽ ነው።


አሳዳጆቼ ይፈሩ፤ እኔን ግን ከዕፍረት ጠብቀኝ፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔን ግን ከድንጋጤ ሰውረኝ፤ ክፉ ቀን አምጣባቸው፤ በዕጥፍ ድርብ ጥፋት አጥፋቸው።


ጻድቁን የምትፈትን ልብንና አእምሮን የምትመረምር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን ለአንተ አሳልፌ ሰጥቻለሁና ስትበቀላቸው ለማየት አብቃኝ።


ሞዓብ ትጠፋለች፤ ከተሞቿም ይወረራሉ፤ ምርጥ ወጣቶቿም ወደ መታረድ ይወርዳሉ፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ፤


ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤ ወደ መታረጃም ይውረዱ! የሚቀጡበት ጊዜ፣ ቀናቸው ደርሷልና ወዮላቸው!


በባቢሎን ምድር ታርደው፣ በአደባባዮቿም እስከ ሞት ቈስለው ይወድቃሉ።


ሦስተኛም ጊዜ፣ “የዮና ልጅ፣ ስምዖን ሆይ፤ ትወድደኛለህን?” አለው። ጴጥሮስም ሦስተኛ ጊዜ ኢየሱስ፣ “ትወድደኛለህን?” ብሎ ስለ ጠየቀው ዐዝኖ፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “በጎቼን መግብ።


በምድርም ላይ በምቾትና በመቀማጠል ኖራችኋል፤ ለዕርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።


እነዚህ ሰዎች ግን ምንም በማያውቁት ነገር እየገቡ ይሳደባሉ፤ እነርሱም ለመያዝና ለመገደል እንደ ተወለዱ፣ በደመ ነፍስ እንደሚመሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሳት የሚጠፉ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos