ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጐልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ለንጉሣቸው ለሴዴቅያስም አልራራለትም፤ ደናግሉንም አልማረም፤ ሽማግሌዎቻቸውንም ወሰዳቸው፤ ሁሉንም እግዚአብሔር በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
ኤርምያስ 11:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በመዓት እጐበኛቸዋለሁ፤ ጐበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ እኔ እቀጣቸዋለሁ፤ ጕልማሶቻቸው በሰይፍ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እቀጣቸዋለሁ፤ ጉልማሶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ራሴ እቀጣቸዋለሁ፤ ጐልማሶቻቸው በሰይፍ ያልቃሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጎበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፥ |
ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጐልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ለንጉሣቸው ለሴዴቅያስም አልራራለትም፤ ደናግሉንም አልማረም፤ ሽማግሌዎቻቸውንም ወሰዳቸው፤ ሁሉንም እግዚአብሔር በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፤ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፤ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፤ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፤ ጐልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
ኢየሩሳሌምንም በመዐት እንደ ጐበኘሁ፥ እንዲሁ በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እጐበኛለሁ።
ስለዚህ ጐበዛዝቷ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፤ በዚያም ቀን ሰልፈኞች ሁሉ ይወድቃሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሕፃናቱንም በመንገድ፤ ጐልማሶቹንም በአደባባዮቻችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመስኮቶቻችን ወደ ሀገራችን ገብቶአልና።
ሣን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከዋል፤ በሰይፍም ወድቀዋል፤ በረኃብ ገደልሃቸው፤ በቍጣህም ቀን ሳትራራ አረድሃቸው።
“በግብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደድሁባችሁ፤ ጐበዛዝቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፤ በሰፈራችሁም እሳትን ሰድጄ አጠፋኋችሁ፤ በዚህም ሁሉ እናንተ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።