ኤርምያስ 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ለምን ርኵሰትን አደረገች? ስእለት ወይም የተቀደሰ ሥጋ ክፋትሽን ከአንቺ ያስወግዳልን? ወይስ በእነዚህ ታመልጫለሽን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወዳጄ፣ ከብዙዎች ጋራ ተንኰሏን እየሸረበች፣ በቤቴ ውስጥ ምን ጕዳይ አላት? ስእለት ወይም የመሥዋዕት ሥጋ ቅጣትሽን ሊያስቀርልሽ ይችላልን? እነዚህንስ በመፈጸም፣ ደስተኛ መሆን ትችያለሽን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ክፋትን አብዝታ በመሥራትዋ ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ምን አላት? የተቀደሰ ሥጋ ክፋትሽን ከአንቺ ያስወግዳልን? ከዚያም ደስተኛ ትሆኛለሽን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ እንድላቸው ነገረኝ፦ “እናንተ እኔ የምወዳችሁ ሕዝብ ናችሁ፤ ነገር ግን እንደእነዚህ ያሉ ክፉ ነገሮችን እያደረጋችሁ በዚህ በቤተ መቅደሴ ውስጥ ልትገኙ አይገባም፤ የምታቀርቡልኝም የእንስሶች መሥዋዕት ከጥፋት አይጠብቃችሁም፤ ስለዚህ በቤተ መቅደሴ ውስጥ መደሰታችሁን አቁሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ምን አላት? ስእለት ወይም የተቀደሰ ሥጋ ክፋትሽን ከአንቺ ያስወግዳልን? ወይስ በእነዚህ ታመልጫለሽን? |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የዝሙትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም ላይ አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
“ሂድ፤ እንዲህ ብለህ በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
ከዳተኞች ልጆች ሆይ! እኔ እገዛችኋለሁና ተመለሱ፤ ይላል እግዚአብሔር። አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፤
ከዳተኛዪቱም እስራኤል እንዳመነዘረች አየሁ፤ የፍችዋንም ደብዳቤ በእጅዋ ሰጥቼ ሰደድኋት፤ ጎስቋላ እኅቷ ይሁዳ ግን በዚያ አልፈራችም፤ እርስዋም ደግሞ ሄዳ አመነዘረች።
እግዚአብሔርም፥ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳን፥ እግዚአብሔር እንደሚወድዳቸው አንተም ክፋትና ዝሙት ያለባትን ሴት ውደድ” አለኝ።
ጌታችን ኢየሱስንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገደለት፤ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያለም በታላቅ ቃል ጮኸ፤ እንዳያሠቃየውም ማለደው።