የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
ኤርምያስ 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥም፤ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ። በፊታቸውም አትደንግጥ አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥተህም ያዘዝሁን ሁሉ ንገራቸው፤ አትፍራቸውም፤ አለዚያ በፊታቸው አስፈራሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ በእነርሱ ፊት እንዳላስፈራህ አትፍራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኤርምያስ ሆይ! እኔ የማዝህን ሁሉ እንድትነግራቸው ወደ እነርሱ ለመሄድ ተዘጋጅ፤ እነሆ እነርሱን አትፍራ፤ አለበለዚያ በእነርሱ ፊት የበለጠ እንድትፈራ አደርግሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፥ በፊታቸው እንዳላስፈራህ አትፍራቸው። |
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፥ “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ” ብሎ ነገረው። ኤልያስም ተነሥቶ ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።
ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኑር” አለው።
ነቢዩም ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “ወገብህን ታጥቀህ ይህን የዘይት ቀንድ በእጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገለዓድም ሂድ።
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ይህ ለአንተ ምልክት ይሆንሃል፤ ሕዝቡን ከግብፅ በአወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።
ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከሀገሩ ይለቅቅ ዘንድ ለፈርዖን ይንገረው።
እነሆ በምድሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናቷ ላይ፥ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።
አሳዳጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፤ በሁለት እጥፍ ጥፋት ቀጥቅጣቸው።
የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር።
ኤርምያስም ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “በሰማችሁት ቃል ሁሉ፥ በዚች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እናገር ዘንድ እግዚአብሔር ልኮኛል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቁም፤ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ትነግራቸው ዘንድ ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ተናገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታጕድል።
የኔርዩም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ቤት የእግዚአብሔርን ቃል በመጽሐፉ አነበበ።
“ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነገርሁህንም የመጀመሪያውን ስብከት ስበክላት” አለው።
ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።