አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት፥ መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ” አላቸው።
ያዕቆብ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቼ ሆይ! በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቼ ሆይ፤ ክቡር በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ እንደ መሆናችሁ አድልዎ አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቼ ሆይ! ክቡር በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ በመሆናችሁ፥ አድልዎን አታድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቼ ሆይ! በክብር ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ ከሆናችሁ አንዱ ከሌላው ይበልጣል በማለት በሰው መካከል አድልዎ አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቼ ሆይ፥ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ። |
አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት፥ መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ” አላቸው።
ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤
ወደ እግዚአብሔር መመለስንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለአረማውያን እየመሰከርሁ፤
ከጥቂት ቀንም በኋላ ፊልክስ ከአይሁዳዊት ሚስቱ ከድሩሲላ ጋር መጣ። ልኮም ጳውሎስን አስጠራው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ማመንም የሚናገረውን ነገር ሰማው።
እርሱም እንዲህ አለ፥ “ወንድሞቻችንና አባቶቻችን ሆይ፥ ስሙ፤ የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በሁለት ወንዞች መካከል ሳለ ወደ ካራንም ሳይመጣ ተገለጠለት።
በፍርድም ፊት አትዩ፤ ለትልቁም፥ ለትንሹም በእውነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታድሉ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከብዳችሁ እርሱን ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ፤
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦን አትቀበል፥ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ያሳውራልና፥ የእውነትንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።
በኢየሱስ ክርስቶስ ማመናችሁንና ቅዱሳንንም ሁሉ መውደዳችሁን ከሰማንበት ጊዜ ጀምሮ፥ ስለ እናንተ እንጸልያለን።
አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ ማዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።
የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ።
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ “አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ድኻውንም “አንተስ ወደዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን?
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤
እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።