ድሆችም በውስጣችሁ ይሰማራሉ፤ ድሆች ሰዎችም በሰላም ያርፋሉ፤ ዘራችሁንም ረኃብ ያጠፋቸዋል፤ ከእናንተም የቀሩት ያልቃሉ።
ኢሳይያስ 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሰው ከላሞቹ አንዲት ጊደርንና ሁለት በጎችን ያሳድጋል፤ የአንዲት በግ ወተትም ሁለት ሰዎችን ያጠግባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን፣ አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በግ ብቻ ይተርፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን፤ አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በግ ብቻ ይተርፈዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያም ዘመን አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በጎች ይኖሩታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ሰው አንዲት ጊደርን ሁለት በጎችንም ያሳድጋል፥ |
ድሆችም በውስጣችሁ ይሰማራሉ፤ ድሆች ሰዎችም በሰላም ያርፋሉ፤ ዘራችሁንም ረኃብ ያጠፋቸዋል፤ ከእናንተም የቀሩት ያልቃሉ።
በዚያም የተሰማራው መንጋ እንደ ተተወ መንጋ ይሆናል፤ ምድሩም ለብዙ ዘመን መሰማሪያ ይሆናል፤ በዚያም መንጋው ይሰማራል፤ ያርፋልም።
“ይህም ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የዘራኸውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላቸሁ፤ ታጭዱማላችሁ፤ ወይንንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
የተማረኩ እንደ በሬዎች ይሰማራሉ፤ የተረሱትም ምግባቸውን ሲፈልጉ እንደ በግ ጠቦቶች በማሰማርያቸው ይሰማራሉ።
በሚታረሰውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍርሀት ይመጣል፤ የበጎች መሰማርያ ይሆናል፤ በሬዎችም ይረግጡታል፤ እሾህና ኵርንችትም ያጠፋዋል።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ግን አንዳች ከሌላቸው ከሕዝቡ ድሆች ከፊሎቹን በይሁዳ ሀገር ተዋቸው፤ የወይኑን ቦታና እርሻውንም በዚያ ጊዜ ሰጣቸው።