Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 7:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “በዚያም ዘመን አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በጎች ይኖሩታል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በዚያ ቀን፣ አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በግ ብቻ ይተርፈዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በዚያን ቀን፤ አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በግ ብቻ ይተርፈዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ሰው ከላ​ሞቹ አን​ዲት ጊደ​ር​ንና ሁለት በጎ​ችን ያሳ​ድ​ጋል፤ የአ​ን​ዲት በግ ወተ​ትም ሁለት ሰዎ​ችን ያጠ​ግ​ባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ሰው አንዲት ጊደርን ሁለት በጎችንም ያሳድጋል፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 7:21
8 Referencias Cruzadas  

ምንም ሀብት ያልነበራቸውን ድኾች ብቻ በይሁዳ ምድር ተወ፤ ለእነርሱም የወይን ተክል ቦታዎችንና የሚያርሱት መሬት ሰጣቸው።


የበግ ጠቦቶች፥ ቀድሞ ይሰማሩበት በነበረ ቦታ ይሰማራሉ፤ የሰቡ ፍሪዳዎችና የፍየል ግልገሎች በፈራረሱ ቦታዎች ሣር ይበላሉ።


ከዚህ በኋላ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፦ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የበቀለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ።


የሶርያ ከተሞች ሰው የማይኖርባቸው ባድማዎች ይሆናሉ፤ በጎችና ከብቶች በዚያ ይሰማራሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።


ቀድሞ በዶማ ተቈፍረው እህል ይበቅልባቸው የነበሩ ኰረብቶች ሁሉ ኲርንችትንና እሾኽን በመፍራት ማንም ወደዚያ አይሄድም፤ ነገር ግን የከብትና የበግ መንጋ መሰማሪያ ብቻ ይሆናሉ።”


እጅግ የደኸዩ መጠጊያ ያገኛሉ፤ ድኽነት ያጠቃቸውም ተዝናንተው ይኖራሉ፤ የእናንተን ልጆች ግን በራብ እገድላለሁ፤ የተረፋችሁትንም አጠፋለሁ።


የተመሸገችው ከተማ ፈራርሳለች፤ ባዶዋን ቀርታ ጭው ያለ ምድረ በዳ መስላለች፤ የከብቶች መሰማሪያ ስለ ሆነች በዚያ ጥጆች የዛፍ ቅርንጫፎችን እየበሉ ያርፋሉ።


በረሓውና ደረቁ ምድር ደስ ይለዋል፤ በምድረ በዳም አበቦች ያብባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios