አካዝም፥ “አልለምንም፤ አምላኬ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ።
አካዝ ግን፣ “አልለምንም፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ።
አካዝ ግን፤ አልለምንም፤ ጌታንም አልፈታተንም” አለ።
አካዝ ግን “ምልክት ስጠኝ ብዬ አልጠይቅም፤ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ።
አካዝም፦ አልለምንም፥ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም አለ።
ንጉሡም አካዝ፥ “የሚቃጠለውን የጥዋት መሥዋዕት፥ የማታውንም የእህሉን ቍርባን፥ የንጉሡንም መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሕዝቡንም ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን፥ የመጠጡንም ቍርባን በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ደም ሁሉ፥ የሌላውንም መሥዋዕታቸውን ደም ሁሉ በእርሱ ላይ ርጭበት፤ የናሱ መሠዊያ ግን በየጥዋቱ ለእኔ ይሁን” ብሎ ካህኑን ኦርያን አዘዘው።
ዳግመኛም ንጉሡ አካዝ ፈጽሞ ከእግዚአብሔር ራቀ።
“ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለአንተ ለምን።”
እርሱም አለ፥ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? እግዚአብሔርን ታደክማላችሁ፤
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፣ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።
ጴጥሮስም፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን መንፈስ ትፈታተኑት ዘንድ እንዴት ተባበራችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግሮች በበር ናቸው፤ አንቺንም ይወስዱሻል” አላት።
ከእነርሱም አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን እንደ ተፈታተኑት፥ ነዘር እባብም እንደ አጠፋቸው እግዚአብሔርን አንፈታተን።
“በፈተና ቀን እንደ ፈተንኸው አምላክህ እግዚአብሔርን አትፈታተነው።