Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ከጥ​ልቁ ወይም ከከ​ፍ​ታው ቢሆን ከአ​ም​ላ​ክህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምል​ክ​ትን ለአ​ንተ ለምን።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ለምን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ‘ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከጌታ ከአምላክህ ለምን።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ከምድር ጥልቀትም ሆነ ከሰማይ ከፍታ አንድ ምልክት እንዲሰጥህ አምላክህን እግዚአብሔርን ለምን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 7:11
18 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ቀን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠ​ዊ​ያው ይሰ​ነ​ጠ​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ይፈ​ስ​ሳል” ብሎ ምል​ክት ሰጠ።


“ይህም ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በዚህ ዓመት የገ​ቦ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ለህ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ለህ፤ ታጭ​ድ​ማ​ለህ፥ ወይ​ንም ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ለህ።


“ፈር​ዖን፦ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን አሳ​ዩኝ ሲላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ወስ​ደህ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባ​ብም ትሆ​ና​ለች።”


“ይህም ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ በዚህ ዓመት የዘ​ራ​ኸ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ላ​ቸሁ፤ ታጭ​ዱ​ማ​ላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ትተ​ክ​ላ​ላ​ችሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምል​ክቱ ምን​ድን ነው?” ብሎ ነበር።


በእ​ሾ​ህም ፋንታ ጥድ፥ በኵ​ር​ን​ች​ትም ፋንታ ባር​ሰ​ነት ይበ​ቅ​ላል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በማ​ይ​ጠፋ ምል​ክት ይመ​ሰ​ገ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ አካ​ዝን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


አካ​ዝም፥ “አል​ለ​ም​ንም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ታ​ተ​ንም” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸ​ክላ ሠሪ የሠ​ራ​ውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከካ​ህ​ናት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤


“ገም​ቦ​ው​ንም ከአ​ንተ ጋር በሚ​ሄዱ ሰዎች ፊት ትሰ​ብ​ራ​ለህ፤


“ቃሌም በላ​ያ​ችሁ ለክ​ፋት እን​ዲ​ጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እን​ደ​ም​ጐ​በ​ኛ​ችሁ ምል​ክ​ታ​ችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለእ​ና​ን​ተም ምል​ክቱ እን​ዲህ ነው፦ ሕፃን አውራ ጣቱን ታስሮ፥ በጨ​ር​ቅም ተጠ​ቅ​ልሎ በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ ታገ​ኛ​ላ​ቸሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos