እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው።
ኢሳይያስ 58:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከድሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎችህ ይሠራሉ፤ መሠረትህም ለልጅ ልጅ ዘመን ይሆናል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድንም አዳሽ ትባላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወገኖችህ የቀድሞ ፍርስራሾችን መልሰው ይሠራሉ፤ የጥንቱንም መሠረት ያቆማሉ፤ አንተም፣ የተናዱ ቅጥሮችን ዐዳሽ፣ ባለአውራ መንገድ ከተሞችን ጠጋኝ ትባላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የአውራ መንገድ አዳሽ ትባላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝባችሁ ቀድሞ ፈራርሰው የነበሩትን ሁሉ እንደገና መልሶ በጥንቱ መሠረት ላይ ይሠራል፤ ስለዚህም እናንተ ‘ቅጽሮችን መልሶ የሚያንጽና ፈራርሰው የነበሩ ቤቶችን የሚያድስ ሕዝብ’ ተብላችሁ ትጠራላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፥ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድ አዳሽ ትባላለህ። |
እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው።
ንጉሡንም፥ “ንጉሡን ደስ ቢያሰኝህ፥ ባሪያህም በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፥ እሠራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባቶች መቃብር ከተማ ስደደኝ” አልሁት።
እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍራሹም አንዳች እንዳልቀረበት ሰንባላጥና ጦቢያ ዓረባዊውም ጌሳም የቀሩትም ጠላቶቻችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን አላቆምሁም ነበር።
ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆንባችኋል።
ቂሮስንም፥ “ብልህ ሁን፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስንም እመሠርታለሁ ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” ይላል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በተመረጠችው ዕለት ሰምቼሃለሁ፤ ድኅነት በሚደረግበትም ቀን ረድቼሃለሁ፤ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትን ርስቶች ትወርስ ዘንድ፤
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ደስ አሰኝሻለሁ፤ ባድማሽንም ሁሉ ደስ አሰኛለሁ፤ ምድረ በዳሽንም እንደ ዔድን፥ በረሃዎችሽንም እንደ እግዚአብሔር ገነት አደርጋለሁ። ደስታና ተድላ እምነትና የዝማሬ ድምፅ በውስጧ ይገኝባታል።
ከጥንት ጀምሮ የፈረሱትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ያድሳሉ።
“ከአናምሄል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ዘመን እነሆ ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ወደ ተሰበረው ቅጥር አልወጣችሁም፤ በእግዚአብሔርም ቀን በሰልፍ ትቆሙ ዘንድ ለእስራኤል ቤት ቅጥርን አልሠራችሁም።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከኀጢአታችሁ ሁሉ በአነጻኋችሁ ጊዜ በከተሞች ሰዎችን አኖራለሁ፤ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ።
ስለዚህ፥ እናንተ የእስራኤል ተራሮች ሆይ! የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆዎች፥ ለምድረ በዳዎች፥ ባዶ ለሆኑትና ለፈረሱት፥ በዙሪያ ላሉት ለቀሩት አሕዛብ ምርኮና መሣለቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል፦
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ቤት አነሣለሁ፤ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፤ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤
የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፤ የፈረሱትንም ከተሞች ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፤ የወይን ጠጃቸውንም ይጠጣሉ፤ ተክልን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።