ኢሳይያስ 52:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ደስ ይበላቸው፤ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ኢየሩሳሌምን አድኖአታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷል፤ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፥ ጌታ ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፥ በአንድነትም ዘምሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል ኢየሩሳሌምንም ይታደጋል ስለዚህ እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ! ተባብራችሁ በደስታ ዘምሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፥ በአንድነትም ዘምሩ። |
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዝአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተቤዥችሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።
እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ምሕረትን አድርጎአልና ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና የምድር መሠረቶች መለከትን ይንፉ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በውስጣቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።
የባርያውን ቃል ያጸናል፤ የመልእክተኞቹንም ምክር ይፈጽማል። ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፤ የይሁዳንም ከተሞች ትታነጻላችሁ፤ ምድረ በዳዎችዋም ይለመልማሉ፤” ይላል፤
ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
እኔ ነኝ፤ የማጽናናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እንግዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ነውን?
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ደስ አሰኝሻለሁ፤ ባድማሽንም ሁሉ ደስ አሰኛለሁ፤ ምድረ በዳሽንም እንደ ዔድን፥ በረሃዎችሽንም እንደ እግዚአብሔር ገነት አደርጋለሁ። ደስታና ተድላ እምነትና የዝማሬ ድምፅ በውስጧ ይገኝባታል።
እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሐሤትም ትማራላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በደስታ ሊቀበሏችሁ ይዘላሉ፤ የሜዳም ዛፎች ሁሉ በቅርንጫፎቻቸው ያጨበጭባሉ።
ከጥንት ጀምሮ የፈረሱትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ያድሳሉ።
በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው።
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።
“የማትወልድ መካን ደስ ይላታል፤ ምጥ የማታውቀውም ደስ ብሎአት እልል ትላለች፤ ባል ካላት ይልቅ የፈቲቱ ልጆች ብዙዎች ናቸውና” ተብሎ ተጽፎአል።