ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች መነሣሣት ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል” አለው።
ኢሳይያስ 52:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አቆማችሁ?” ይላል እግዚአብሔር፤ “ታደንቃላችሁ፤ ትጮሃላችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ስሜም በእናንተ ምክንያት በአሕዛብ ዘንድ ሁልጊዜ ይሰደባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁን እዚህ ምን አለኝ?” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕዝቤ ያለ ምክንያት ተወስዷል፤ የገዟቸው ተሣልቀውባቸዋል” ይላል እግዚአብሔር። “ቀኑን ሙሉ፣ ስሜ ያለ ማቋረጥ ይሰደባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል ጌታ፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል ጌታ፥ ስሜም ያለማቋረጥ በየእለቱ ቀኑን ሙሉ ይሰደባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝቤ ያለ ዋጋ ሲወሰድ እያየሁ አሁን እኔ የማደርገው ምን አለ? ገዢዎቻቸውም ይሳለቁባቸዋል፤ ያለማቋረጥም ስሜን ይሰድባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፥ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል። |
ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች መነሣሣት ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል” አለው።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
መቃብር በዚያ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ስፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖርያ ያሳነጽህ ወደዚህ ለምን መጣህ? ለምንስ በዚህ ተደፋፈርህ?
ኢሳይያስ፥ “ለጌታችሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች ስለ ሰደቡኝ፥ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል።
ልጆችሽ ዝለዋል፤ እንደ ጠወለገ ቅጠልም በየመንገዱ ዳር ወድቀዋል፤ በአምላክሽ በእግዚአብሔር ቍጣና ተግሣጽ ተሞልተዋል።
ወደ በደሉሽና ወደ አጐሰቈሉሽ ሰዎች እጅ፥ ሰውነትሽንም ዝቅ በዪ፥ ድልድይ አድርገን እንሻገርብሽ ወደሚሏት ሰዎች እጅ እመልሰዋለሁ።” በምድርም ላይ በሆድሽ አስተኙሽ፤ መንገደኞችም ሁሉ ረገጡሽ።
“እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።”
ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
ጋሜል። በጽኑ ቍጣው የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ቀጠቀጠ፤ ቀኝ እጁንም ከጠላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፤ እንደ እሳት ነበልባል ያዕቆብን አቃጠለ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ በላ።
ነገር ግን በመካከላቸው በአሉ፥ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
በሚካ ቤትም በነበሩ ጊዜ የሌዋዊዉን የጐልማሳውን ድምፅ ዐወቁ፤ ወደ እርሱም ቀርበው፥ “ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህስ የምታደርገው ምንድን ነው? በዚህስ ምን አለህ?” አሉት።