አክዓብም ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ወደ ኢይዝራኤላዊው ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወርሰው ተነሥቶ ወረደ።
ኢሳይያስ 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይን ጠጅ ለሚጠጡ ኀያላን፥ የሚያሰክረውንም መጠጥ ለሚደባልቁ ጽኑዓን ወዮላቸው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፣ የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፤ የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ጠጅ በመጠጣት ጀግኖች፥ የሚያሰክረውንም መጠጥ ለማደባለቅ ደፋሮች ለሆኑ ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይን ጠጅ ለመጠጣት ኃያላን የሚያሰክረውንም ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፥ |
አክዓብም ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ወደ ኢይዝራኤላዊው ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወርሰው ተነሥቶ ወረደ።
እነሆም፥ በዓልን፥ ደስታንና ሐሴትን አደረጋችሁ፤ በሬዎችንና በጎችንም አረዳችሁ፤ “ነገ እንሞታለን፤ እንብላ፤ እንጠጣም፤” እያላችሁ ሥጋን በላችሁ፤ ወይንንም ጠጣችሁ።
እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ።
ኑ፤ የወይን ጠጅ እንውሰድ፤ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፤ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።