ኢሳይያስ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን የወይኔን ቦታ በተመለከተ የወዳጄን መዝሙር ለወዳጄ እዘምራለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ቦታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ወዳጄ፣ ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ ወዳጄ በለምለም ኰረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ ስለ ወዳጄ፤ ወዳጄ በለምለም ኮረብታ ላይ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ወይኑ ተክል ለውዴ የፍቅር ዘፈን ልዝፈን ውዴ እጅግ ለም በሆነ ኰረብታ ላይ የወይን ተክል ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ስለ ወዳጄና ስለ ወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ኮረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው። |
ጕሮሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለንተናውም የተወደደ ነው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ልጅ ወንድሜ ይህ ነው፥ ወዳጄም ይህ ነው።
እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወንድሜ ቃል ደጅ እየመታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።
ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፤ እድል ፈንታዬንም አርክሰዋል፤ የምወድዳትንም እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገዋታል።
እኔ የተመረጠች ወይን፥ ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንዴት መራራ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?
“እናትህ በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለች እንደ ወይን ግንድና እንደ ጽጌረዳ ነበረች፤ ከውኃም ብዛት የተነሣ የምታፈራና የምትሰፋ ሆነች።
እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዉን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን ሠርተዋል።
“ሌላ ምሳሌ ስሙ። የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፤ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
ለሕዝቡም ይህን ምሳሌ ይመስልላቸው ጀመረ፤ እንዲህም አላቸው፥ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ መጭመቂያም አስቈፈረ፤ ግንብም ሠራለት፤ ለገባሮችም ሰጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ ሳይመለስም ዘገየ።
አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካምና ሰፊ ምድር፥ ከሜዳና ከተራሮች የሚመነጩ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾችም ወዳሉባት ምድር፥