La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 48:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁሉን ሰም​ተ​ሃ​ሃል፤ አላ​ወ​ቅ​ህም፤ ከዛሬ ጀምሮ የሚ​ሆ​ነ​ውን አዲስ ነገር ገለ​ጥ​ሁ​ልህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህን ነገሮች ሰምተሃል፤ ሁሉንም ተመልከታቸው፤ ራስህ ትክክለኛነታቸውን አትመሰክርምን? “ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣ የተሰወሩብህን ያላወቅሃቸውን ነገሮች እነግርሃለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰምተሃል፤ አሁን ይህን ሁሉ ተመልከት፤ ይሄን ራስህ አትመሰክርም? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲስ ነገሮችን ከአሁን ጀምሬ አሳይችኋለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እኔ የተናገርኩትን ሰምታችኋል፤ ይህም መፈጸሙን አይታችኋል፤ አስተውሉትና እውነተኛነቱን አረጋግጡ፤ ከአሁን ጀምሮ ቀድሞ ተሰውሮ የነበረ እናንተ ያላወቃችሁትን አዲስ ነገር ወደፊት አሳያችኋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰምተሃል፥ ይህን ሁሉ ተመልከት፥ እናንተም የምትናገሩት አይደላችሁምን? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲሶች ነገሮችን ከዚህ ጀምሬ አሳይቼሃለሁ።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 48:6
29 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ የተ​ረ​ፋ​ች​ሁና መከራ የም​ት​ቀ​በሉ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረ​ኝ​ንና የሰ​ማ​ሁ​ትን ስሙ።


ብዙ ነገ​ርን ታያ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን አት​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትም፤ ጆሮ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ተከ​ፍ​ተ​ዋል፤ ነገር ግን አት​ሰ​ሙም።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብ​ሬን ለሌላ፥ ምስ​ጋ​ና​ዬ​ንም ለተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች አል​ሰ​ጥም።


እነሆ የቀ​ድ​ሞው ነገር ተፈ​ጸመ፤ አዲስ ነገ​ር​ንም እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም ሳይ​ነ​ገር እር​ሱን አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።”


እነሆ፥ አዲስ ነገ​ርን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እር​ሱም አሁን ይበ​ቅ​ላል፤ እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ በም​ድረ በዳም መን​ገ​ድን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም አሁን እንጂ ከጥ​ንት አል​ተ​ፈ​ጠ​ሩም፤ አን​ተም፥ “እነሆ፥ ዐው​ቄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ” እን​ዳ​ትል ከዛሬ በፊት አል​ሰ​ማ​ሃ​ቸ​ውም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨ​ለ​መች ምድር ሆን​ሁ​በ​ትን? ሕዝ​ቤስ ስለ ምን፦ እኛ አን​ገ​ዛ​ል​ህም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ወደ አንተ አን​መ​ለ​ስም ይላል?


ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


ወይስ በከ​ተማ ውስጥ መለ​ከት ሲነፋ ሕዝቡ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ክፉ ነገር በከ​ተማ ላይ ይመ​ጣ​ልን?


የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፥ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፥ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ።


በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።


እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ና​ንተ ላይ በወ​ረደ ጊዜ ኀይ​ልን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ሁሉ፥ በሰ​ማ​ር​ያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረ​ስም ምስ​ክ​ሮች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ።”


ነገር ግን መጽ​ሐፍ፥ “ዐይን ያላ​የው፥ ጆሮም ያል​ሰ​ማው፥ በሰ​ውም ልቡና ያል​ታ​ሰበ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዱት ያዘ​ጋ​ጀው ነው።” ብሎ የለ​ምን?


እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።


ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።