ኢሳይያስ 44:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የሚረዳህም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፥ “ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ወዳጄ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈጠረህ፣ በማሕፀን የሠራህ፣ የሚረዳህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህ ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የሚረዳህም ጌታ እንዲህ ያልል፦ አገልጋዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ይሹሩን ሆይ፥ አትፍራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማሕፀን የሠራኋችሁና የምረዳችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ አገልጋዮቼ ስለ ሆናችሁና እኔ ስለ መረጥኳችሁ አትፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የሚረዳህም እግዚአብሔር እንዲህ ያልል፦ ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ይሹሩን ሆይ፥ አትፍራ። |
ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቍጥር ጥቂት የነበርህ እስራኤል ሆይ፥ እኔ እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዝአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተቤዥችሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ አገልጋዬ ነህና ይህን ዐስብ፤ እኔ ፈጥሬሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ አትርሳኝ።
ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብቻዬ የፈጠርሁ፥ ሰማያትን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤
“የእስራኤልም ቅዱስ የሚመጣውንም የፈጠረ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ጠይቁኝ፤ ስለ እጄም ሥራ እዘዙኝ።
ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተም አሕዛብ፥ አድምጡ፤ ከረዥም ዘመን በኋላ እንዲህ ይሆናል ይላል እግዚአብሔር፤ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠርቶአል፤
አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ከብሬአለሁና፥ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ፥ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባርያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የፈጠረኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
“እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከምርኮ ሀገር አድናለሁና ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ ያዕቆብም ይመለሳል፤ ያርፍማል፤ ተዘልሎም ይቀመጣል፤ ማንም አያስፈራውም።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።