Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 44:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አሁ​ንም ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ነገር ግን አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህ እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አሁንም አገልጋዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አድምጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 44:1
22 Referencias Cruzadas  

ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ኃጢ​አት ሠራን፥ ዐመ​ፅ​ንም፥ በደ​ል​ንም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን ይም​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ ይመ​ር​ጠ​ዋል፤ በሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ፤ መጻ​ተ​ኞ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ጋር ይጨ​መ​ራሉ።


ባሪ​ያዬ እስ​ራ​ኤል፥ የመ​ረ​ጥ​ሁህ ያዕ​ቆብ፥ የወ​ዳጄ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሆይ፥


አንተ ከም​ድር ዳርቻ የያ​ዝ​ሁህ፥ ከማ​ዕ​ዘ​ን​ዋም የጠ​ራ​ሁህ ነህና፦ አንተ ባሪ​ያዬ ነህ፤ መር​ጬ​ሃ​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፤ ያል​ሁህ ሆይ፥


ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ምጥ፥ ለሚ​መ​ጣ​ውም ጊዜ የሚ​ሰማ ማን ነው?


አሁ​ንም ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የፈ​ጠ​ረህ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ የሠ​ራህ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ በስ​ም​ህም ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አን​ተም እስ​ራ​ኤል፥ አገ​ል​ጋዬ ነህና ይህን ዐስብ፤ እኔ ፈጥ​ሬ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ባሪ​ያዬ ነህ፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አት​ር​ሳኝ።


ስለ አገ​ል​ጋዬ ስለ ያዕ​ቆብ፥ ስለ መረ​ጥ​ሁ​ትም ስለ እስ​ራ​ኤል ብዬ በስ​ምህ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ተቀ​በ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የጠ​ራ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ፊተ​ኛው ነኝ፤ እኔም ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ነኝ።


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከም​ርኮ ሀገር አድ​ና​ለ​ሁና ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ ያዕ​ቆ​ብም ይመ​ለ​ሳል፤ ያር​ፍ​ማል፤ ተዘ​ል​ሎም ይቀ​መ​ጣል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም።


አን​በሳ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ቶ​አል፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው የሚ​ዘ​ርፍ ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ምድ​ር​ሽን ባድማ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ሽ​ንም ሰው እን​ዳ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ያፈ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ከስ​ፍ​ራው ወጥ​ቶ​አል።


“ነቢ​ያ​ትን የም​ት​ገ​ድ​ሊ​ያ​ቸው፥ ወደ አንቺ የተ​ላ​ኩ​ትን ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም የም​ት​ደ​በ​ድ​ቢ​ያ​ቸው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዶሮ ጫጩ​ቶ​ች​ዋን ከክ​ን​ፍዋ በታች እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ ልጆ​ች​ሽን ልሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ምን ያህል ወደ​ድሁ? ነገር ግን እንቢ አላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos