ኢሳይያስ 34:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያላን ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትሰክራለች፤ በስባቸውም ትወፍራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጐሽ ዐብሯቸው፣ ኰርማም ከወይፈን ጋራ ይወድቃል፤ ምድራቸው በደም ትርሳለች፤ ዐፈራቸውም ሥብ በሥብ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጎሽ ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትርሳለች፥ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤዶም ሕዝብ እንደ ጐሽ፥ እንደ ኰርማና እንደ ወይፈን ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ከሌሎች ጋር አብረው ይሞታሉ፤ ሀገሪቱም በደማቸው ትነከራለች፤ ምድሪቱም በስባቸው ትዳብራለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጎሽ ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፥ ምድራቸውም በደም ትረካለች፥ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች። |
ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደ የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች! አልቅሱ፤ እናንተም የበጎች አውራዎች! ጩኹ።
በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች በእርስዋ ተቀልበው እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፤ በአንድነትም ሸሹ፤ አልቆሙምም።
“ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤
ፍሬዋን ሁሉ አድርቁባት፤ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው ደርሳለችና፥ እነሱን የሚበቀሉበት ጊዜ ደርሷልና ወዮላቸው!
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ ኑ፤ ተከማቹ፤ ሥጋንም ትበሉ ዘንድ፥ ደምንም ትጠጡ ዘንድ በእስራኤል ተራሮች ላይ ወደማርድላችሁ መሥዋዕት፥ እርሱም ታላቅ መሥዋዕት፥ ከየሰፍራው ሁሉ ተሰብሰቡ።
የኀያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም አለቆች፥ የአውራ ፍየሎችንና የአውራ በጎችን፥ የወይፈኖችንና፥ የባሳንን ፍሪዳዎች ሁሉ፥ ደም ትጠጣላችሁ።
እግዚአብሔር ከግብፅ መርቶ አውጥቶታል፤ አንድ ቀንድ እንዳለው ክብር አለው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፤ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፤ በፍላጾቹም ጠላቱን ይወጋዋል።
ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፤ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፤ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።