እርሱም፥ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ተመልሶ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፤ እንዲህ ሲል፦
ኢሳይያስ 18:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት ምድር ወዮላት! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢትዮጵያ ወንዞች ዳር ለምትገኝ፣ ፉር ፉር የሚሉ ክንፎች ላሉባት ምድር ወዮላት! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የክንፎች ድምፅ ለሚሰማባት አገር ወዮላት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት፥ |
እርሱም፥ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ተመልሶ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፤ እንዲህ ሲል፦
ርዳታ ለመፈለግ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፥ በፈረሶችና በሰረገሎችም ለሚታመኑ ወዮላቸው! ፈረሰኞቹ ብዙዎች ናቸውና፤ በእስራኤልም ቅዱስ አልታመኑምና፤ እግዚአብሔርንም አልፈለጉምና።
እርሱም፥ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቶአል” የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፤ እንዲህ ሲል፦
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ግብፅና የኢትዮጵያ ንግዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይገዙልሃል፤ እጆቻቸውን ታስረው በኋላህ ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፤ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።
በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ በግብፅም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ፥ ይመጣልና።
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።