እናንተ የጌላቡሄ ተራሮች ሆይ፥ ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፤ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ። የኀያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና፤ የሳኦልም ጋሻ ዘይት አልተቀባምና።
ኢሳይያስ 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፤ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐሴቦን ዕርሻ፣ የሴባማም የወይን ተክል ጠውልጓል፤ የአሕዛብ ገዦች፣ ኢያዜርን ዐልፈው፣ ምድረ በዳውን ዘልቀው፣ ሥሮቻቸውን እስከ ባሕር ሰድደው የነበሩትን የተመረጡ የወይን ተክሎችን ረጋግጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች ኢያዜርን አልፈው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፤ ቁጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሀሴቦን እርሻዎችና የሲብማ የወይን ተክል ቦታዎች ተደምስሰዋል፤ እነዚህ የወይን ተክል ቦታዎች የአሕዛብ መሪዎችን የሚያሰክር የወይን ጠጅ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ነበሩ፤ ከዚያ በፊት የእነዚያ የወይን ተክሎች ሐረግ እስከ ያዕዜር ከተማ ድረስ የተንሰራፋ ነበር፤ እንዲሁም በስተ ምዕራብ እስከ ሙት ባሕር ማዶና በስተ ምሥራቅም እስከ በረሓው ይደርስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፥ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር። |
እናንተ የጌላቡሄ ተራሮች ሆይ፥ ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፤ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ። የኀያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና፤ የሳኦልም ጋሻ ዘይት አልተቀባምና።
እርሱ በልቡ እንዲህ አይመስለውም፤ እንዲህም አያስብም፤ ነገር ግን ማጥፋት፥ ጥቂት ያይደሉትንም አሕዛብ መቍረጥ በልቡ አለ።
ስለዚህ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ ዛፎችሽ ወድቀዋል፤ የዛፍሽን ፍሬና የወይንሽን መከር እረግጣለሁ፤ ተክሎችሽ ሁሉ ይወድቃሉ።
አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ! የኢያዜርን ልቅሶ ለአንቺ አለቅሳለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፤ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፤ ሳይበስል በሰብልሽና በወይንሽ ላይ ጥፋት መጥቶአል።
ሙሴም ሰላዮቹን ወደ ኢያዜር ላከ፤ እርስዋንና መንደሮችዋንም ያዙ፤ በዚያም የነበሩትን አሞሬዎናውያንን አባረሩ።
ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በራባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥