ኢሳይያስ 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ስለዚህ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ ዛፎችሽ ወድቀዋል፤ የዛፍሽን ፍሬና የወይንሽን መከር እረግጣለሁ፤ ተክሎችሽ ሁሉ ይወድቃሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ስለዚህ ስለ ሴባማ የወይን ተክል፣ ኢያዜር እንዳለቀሰች፣ እኔም አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦን ሆይ፤ ኤልያሊ ሆይ፤ በእንባዬ አርስሻለሁ! ፍሬ ባፈራሽበት ወቅት የነበረው ሆታ፣ መከርሽም ሲደርስ የነበረው ደስታ ተቋርጧልና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ስለዚህ ስለ ሴባማ የወይን ግንድ ከኢያዜር ልቅሶ ጋር አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ በዛፍሽ ፍሬና በወይንሽ መከር የጦር ጩኸት ወድቆአልና በእንባዬ አርስሻለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ስለ ያዕዜር እንደማለቅስ ስለ ሲብማ የወይን ሐረጎችም አለቅሳለሁ፤ ስለ ሐሴቦንና ስለ ኤልዓሌ እንባዬ ይረግፋል፤ ሕዝቡ የሚደሰትበት መከር አልተገኘባቸውም፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ስለዚህ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ የወይን ግንድ አለቅሳለሁ፥ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ በዛፍሽ ፍሬና በወይንሽ መከር የጦር ጩኸት ወድቆአልና በእንባዬ አረካሻለሁ። Ver Capítulo |