ኢሳይያስ 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞዓብን ትዕቢትና እጅግ መኵራቱን ሰምተናል፤ ትዕቢቱንም አስወገድሁ፤ ጥንቈላህ እንዲህ አይደለምና፥ እንዲህም አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞዓብን መዘባነን፣ እጅግ መታበዩንና ኵራቱን፣ እብሪቱንና ስድነቱን ሰምተናል፤ ትምክሕቱ ግን ከንቱ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞዓብን ኩራት፥ እጅግ መታበዩን! ስለ እብሪቱና ስለ ኩራቱ፥ ስለ ስድነቱም ሰምተናል፤ ትምክሕቱ ከንቱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “የሞአብ ሕዝብ ምን ያኽል ኩራተኛ መሆኑን፥ ትዕቢተኛነቱን፥ ዕብሪተኛነቱንና ንቀቱን ሰምተናል፤ ነገር ግን ፉከራው ሁሉ ከንቱ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሞዓብ ትዕቢት እጅግ ስለ መታበዩ፥ ስለ ኵራቱና ስለ ትዕቢቱ ስለ ቍጣውም ሰምተናል፥ ትምክሕቱ ከንቱ ነው። |
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረፍትን ይሰጠናል፤ እህልም በመንኰራኵር ጭድም በጭቃ እንደሚበራይ እንዲሁ ሞዓብ ይረገጣል።
እናንተም “ከሲኦል ጋር ተማምለናል፤ ከሞትም ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፤ ሐሰትንም መሸሸጊያን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና፥ ዐውሎ ነፋስም ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ትላላችሁና፥
ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፤ ከኢኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም፤ የሚያልፍ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ ይረግጣችኋል፤ ትደክማላችሁም።
በሟርት ሙት እናስነሣለን የሚሉትን፥ ከልባቸውም አንቅተው ሐሰት የሚናገሩትን ሰዎች ምልክት የሚለውጥ ማን ነው? ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ ይመልሳል፤ ምክራቸውንም ስንፍና ያደርጋል።
“በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና፥ አስክሩት፤ ሞአብም በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤ በእጁም ያጨበጭባል፤ ደግሞ መሳቂያ ይሆናል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የኤዶምያስን ንጉሥ አጥንት አመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎታልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞዓብ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።