ኢሳይያስ 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርም ሁሉ ዐርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች፤ እልልም ብላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ሁሉ ሰላምና ዕረፍት አግኝታለች፤ የደስታም ዝማሬ ታስተጋባለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርም ሁሉ አርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች እልልም ብላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻ ግን እነሆ ዓለም ሁሉ የሰላም ዕረፍት ያገኛል፤ ሁሉም በደስታ ይዘምራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርም ሁሉ አርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች እልልም ብላለች። |
ከባድ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው ይወነጅላል፤ በደለኛውም ይበድላል። የኤላም ሰዎችና የሜዶን መልእክተኛ በእኔ ላይ ይመጣሉ። ዛሬ ግን እጨነቃለሁ፤ እረጋጋለሁም።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር፥ በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን ደስ ይላቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።
በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረውን የእግዚአብሔርን መልአክ፦ በምድር ላይ ተመላለስን፥ እነሆም፥ ምድር ሁሉ ዝም ብላ ዐርፋ ተቀምጣለች ብለው መለሱለት።