ኢሳይያስ 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እጅ ሁሉ ትዝላለች፤ ሰውም ሁሉ ይደነግጣል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፍርሃት የተነሣ የእያንዳንዱ ሰው እጅ ይዝላል፤ የእያንዳንዱም ሰው ልብ በፍርሃት ይዋጣል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እጅ ሁሉ ትዝላለች፥ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል። |
ስለ ግብፅ የተነገረ ራእይ። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም የእጆቻቸው ሥራዎች በፊቱ ይዋረዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።
ልጆችሽ ዝለዋል፤ እንደ ጠወለገ ቅጠልም በየመንገዱ ዳር ወድቀዋል፤ በአምላክሽ በእግዚአብሔር ቍጣና ተግሣጽ ተሞልተዋል።
የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
የሰው ልጅ ሆይ! በሕዝቤ ላይ ነውና፥ በእስራኤልም አለቆች ሁሉ ላይ ነውና ጩኽ፤ ዋይም በል፤ እነርሱ ከሕዝቤ ጋር ለሰይፍ ተሰጥተዋል፤ ስለዚህ እጅህን ጽፋ።
እነርሱም፦ ስለ ምን ታለቅሳለህ? ቢሉህ አንተ እንዲህ በላቸው፦ ስለሚመጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀልጣል፤ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፤ ሥጋና መንፈስ ሁሉ ይደክማል፤ ከጕልበትም እዥ ይፈስሳል፤ እነሆ ይመጣል፤ ይፈጸማልም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ይህንም ነገር ሰምተን በልባችን ደነገጥን፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእኛ የአንዱም እንኳን ነፍስ አልቀረም።