ደግሞም በቤቴል ኮረብታ የነበረውን መሠዊያ፥ እስራኤልንም ያሳተ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያሠራውን የኮረብታውን መስገጃ፥ ይህንም መሠዊያና መስገጃ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹንም ሰባበረ፤ አድቅቆም ትቢያ አደረገው፤ የማምለኪያ ዐፀዱንም አቃጠለው።
ሆሴዕ 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ደግሞ በእስራኤል ዘንድ ነው፤ ሠራተኛ ሠራው፤ እርሱም አምላክ አይደለም፤ ሰማርያ ሆይ! እንቦሳሽ ተቅበዝብዞአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም በእስራኤል ሆነ! የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክ አይደለም፤ ያ የሰማርያ ጥጃ፣ ተሰባብሮ ይደቅቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተሠራው ነገር ከእስራኤል ዘንድ ነው፤ እርሱም በሞያተኛ የተሠራ ነው፤ እርሱም አምላክ አይደለም፤ የሰማርያም እምቦሳ ይሰባበራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ በጥጃ ምስል የተሠራ ጣዖት በአናጢ እጅ የተሠራ ስለ ሆነ አምላክ ሊሆን አይችልም፤ ስለዚህ በጥጃ ምስል የተሠራው የሰማርያ ጣዖት ተሰባብሮ ይወድቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ደግሞ ከእስራኤል ዘንድ ነው፥ ሠራተኛ ሠራው፥ እርሱም አምላክ አይደለም፥ የሰማርያም እምቦሳ ይቈራረጣል። |
ደግሞም በቤቴል ኮረብታ የነበረውን መሠዊያ፥ እስራኤልንም ያሳተ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያሠራውን የኮረብታውን መስገጃ፥ ይህንም መሠዊያና መስገጃ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹንም ሰባበረ፤ አድቅቆም ትቢያ አደረገው፤ የማምለኪያ ዐፀዱንም አቃጠለው።
በሰማርያም ከተሞች የነበሩትን፥ እግዚአብሔርን ያስቈጡት ዘንድ የእስራኤል ነገሥታት የሠሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ኢዮስያስ አስወገዳቸው፤ በቤቴልም እንዳደረገው ነገር ሁሉ እንዲሁ አደረገባቸው።
አሁንም በዳዊት ልጆች እጅ የሚሆነውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ልትቋቋሙ እንዲህ ትላላችሁ። እናንተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፥ ኢዮርብዓምም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ እንቦሶች ከእናንተ ጋር ናቸው።
ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በይሁዳ ከተሞች የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወጥተው ዐምዶቹን ሰበሩ፤ ዐፀዶችንም ኮረብታዎችንም አፈረሱ፤ መሠዊያውንም አጠፉ። በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን ፈጽመው እስከ ዘለዓለሙ አጠፉአቸው። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።
ሰው ሁሉ ዕውቀት አጥቶ ሰንፎአል፤ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የለውምና።
“ለአሕዛብ ተናገሩ፤ አውሩም፤ ዓላማውንም አንሡ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮዳክ ፈራች፤ ምስሎችዋም አፈሩ፤ ጣዖታቷም ደነገጡ፤ በሉ።
ዳግመኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚሠራው አምሳል ከወርቃቸውና ከብራቸው ጣዖትን ሠሩ፤ እንዲህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አልቋል።”
ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ። እንዲህም በሉት፥ “ኀጢአትን ሁሉ አስወግድ፤ በቸርነትም ተቀበለን፤ በወይፈንም ፈንታ የከንፈራችንን ፍሬ ለአንተ እንሰጣለን።
የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።
የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል?
እንግዲህ እኛ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆን በሰው ዕውቀትና ብልሀት በተቀረጸ በድንጋይና በብር፥ በወርቅም አምላክነቱን ልንመስለው አይገባም።
አሁን ግን እንደምታዩትና እንደምትሰሙት ይህ ጳውሎስ ኤፌሶንን ብቻ ሳይሆን መላውን እስያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝብንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚሠሩትንም ሁሉ አማልክት አይደሉም አላቸው።