ስለዚህ ከዚች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወደ አላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ምሕረትን ለማያደርጉላችሁ ሌሎች አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።”
ሆሴዕ 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬም መሠዊያን አብዝቶአልና የወደደው መሠዊያ ለኀጢአት ሆነበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኤፍሬም ለኀጢአት ማስተስረያ ብዙ መሠዊያዎችን ቢሠራም፣ እነርሱ የኀጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆነውበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬም ኃጢአትን ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቶአልና የኃጢአት መሥርያ መሠዊያዎች ሆነውለታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ ብዙ መሠዊያዎችን ለኃጢአት ማስተስረያ ብለው ሠርተዋል፤ ነገር ግን እነዚያ መሠዊያዎች የኃጢአት መሥሪያ ቦታዎች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬም ኃጢአትን ለመሥራት መሠዊያ አብዝቶአልና መሠዊያ ለኃጢአት ይሆንለታል። |
ስለዚህ ከዚች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወደ አላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ምሕረትን ለማያደርጉላችሁ ሌሎች አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።”
የይሁዳ ኀጢአት በብረት ብርዕ በደንጊያ ሰሌዳ ተጽፎአል፤ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶችም ተቀርጾአል።
የእስራኤል ኀጢአት የሆኑት የአዎን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላም በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ፤ ተራሮችንም፥ “ክደኑን፤ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን” ይሉአቸዋል።
ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ልባቸውን አላቀኑም፤ የዝሙት መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ እግዚአብሔርንም አላወቁትምና።
በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትንም፥ የማይበሉትንም፥ የማያሸቱትንም፥ በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ሌሎች አማልክት ታመልካላችሁ።