Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የይ​ሁዳ ኀጢ​አት በብ​ረት ብርዕ በደ​ን​ጊያ ሰሌዳ ተጽ​ፎ​አል፤ በል​ባ​ቸው ጽላ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ቸው ቀን​ዶ​ችም ተቀ​ር​ጾ​አል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “የይሁዳ ኀጢአት በብረት ብርዕ፣ በሾለ የአልማዝ ጫፍ፣ ተጽፏል፤ በልባቸው ጽላት፣ በመሠዊያቸውም ቀንዶች ላይ ተቀርጿል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብዕር ተጽፎአል፤ በተሾለም ዕብነ አልማዝ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያዎቻችሁ ቀንዶች ተቀርጾአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ኃጢአታችሁ በብረት ብዕር ተጽፎአል፤ ሹል በሆነው አልማዝ በልባችሁ ጽላትና በመሠዊያዎቻችሁ ቀንዶች ላይ ተቀርጾአል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብርዕና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተጽፎአል፥ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ተቀርጾአል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 17:1
15 Referencias Cruzadas  

ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው፤


በጣቶችህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው።


እነሆ፥ እኔ በእጄ ግን​ቦ​ች​ሽን ሣልሁ፤ አን​ቺም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነሽ።


ይሁዳ ሆይ! አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መን​ገ​ዶች ቍጥር ለነ​ው​ረኛ ነገር ለበ​ዓል ታጥ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።


በእ​ን​ዶድ ብት​ታ​ጠ​ቢም፥ ለራ​ስ​ሽም ሳሙና ብታ​በዢ፥ በእኔ ፊት በኀ​ጢ​አ​ትሽ ረክ​ሰ​ሻል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከእ​ነ​ዚያ ወራት በኋላ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጋር የም​ገ​ባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ቡ​ና​ቸው አኖ​ራ​ለሁ፤ በል​ባ​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ትድኚ ዘንድ ልብ​ሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚ​ኖ​ር​ብሽ እስከ መቼ ነው?


ለነ​ቢ​ያ​ትም ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ራእ​ይ​ንም አብ​ዝ​ቻ​ለሁ፤ በነ​ቢ​ያ​ትም እጅ ተመ​ስ​ያ​ለሁ።


ወን​ጀ​ላ​ቸ​ውን አንድ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው እንደ አሰቡ ክፋ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ዐሰ​ብሁ፤ አሁ​ንም ክፋ​ታ​ቸው ከብ​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ በደ​ላ​ቸ​ውም በፊቴ አለች።


ኤፍ​ሬም መሠ​ዊ​ያን አብ​ዝ​ቶ​አ​ልና የወ​ደ​ደው መሠ​ዊያ ለኀ​ጢ​አት ሆነ​በት።


ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፣ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ።


እና​ንተ ራሳ​ች​ሁም በእኛ የተ​ላ​ከች የክ​ር​ስ​ቶስ መል​እ​ክት እንደ ሆና​ችሁ ያው​ቃሉ፤ ይህ​ቺ​ውም የተ​ጻ​ፈች በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው እንጂ በቀ​ለም አይ​ደ​ለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌ​ዳ​ነት ነው እንጂ በድ​ን​ጋይ ሠሌ​ዳም አይ​ደ​ለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos