La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሆሴዕ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን ቀን አለ​ቆች ከወ​ይን ጠጅ ሙቀት የተ​ነሣ ታመሙ፤ እነ​ር​ሱም ከዋ​ዘ​ኞች ጋር እጆ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በንጉሣችን የበዓል ቀን፣ አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤ እርሱም ከፌዘኞች ጋራ ተባበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በንጉሣችን ቀን ሹማምንቱ ከወይን ጠጅ ሞቅታ የተነሣ ታመሙ፤ እርሱም ከፌዘኞች ጋር እጁን ዘረጋ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በንጉሣቸው ክብረ በዓል ቀን መኳንንቱ ብዙ የወይን ጠጅ በመጠጣት ሰክረው ታመሙ፤ ጋጋሪውም ለሚያፌዙ ሰዎች ምልክት ለመስጠት እጁን ዘረጋ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በንጉሣችን ቀን አለቆች ከወይን ጠጅ ሙቀት የተነሣ ታመሙ፥ እርሱም ከዋዘኞች ጋር እጁን ዘረጋ።

Ver Capítulo



ሆሴዕ 7:5
20 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈር​ዖን የተ​ወ​ለ​ደ​በት ዕለት ነበር፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ ግብር አደ​ረገ፤ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹን አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹን አለቃ በአ​ሽ​ከ​ሮቹ መካ​ከል ዐሰበ።


ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በቤ​ቴል ባለው መሠ​ዊያ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ንጉሡ፥ “ያዙት” ብሎ እጁን ከመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አነሣ። ከዚ​ህም በኋላ በእ​ርሱ ላይ የዘ​ረ​ጋት እጁ ደረ​ቀች፤ ወደ እር​ሱም ይመ​ል​ሳት ዘንድ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም።


ምስ​ጉን ነው፥ በዝ​ን​ጉ​ዎች ምክር ያል​ሄደ፥ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መን​ገድ ያል​ቆመ፥ በዋ​ዘ​ኞ​ችም ወን​በር ያል​ተ​ቀ​መጠ ሰው።


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።


ለተሳዳቢና ለሰካራም ወይን ክፉ ነው፥ ጽዋውንም መላልሶ የሚጨልጥ ጠቢብ አይደለም፥ እንደዚህ ያለ አላዋቂም ሁሉ አንድ ይሆናል።


ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰ​ከሩ፥ በወ​ፍ​ራም ተራራ ራስ ላይ ላለ​ችም ለረ​ገ​ፈች ለክ​ብር ጌጥ አበባ ወዮ!


ስለ​ዚህ የተ​ጨ​ነ​ቃ​ችሁ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን ሕዝብ የም​ት​ገዙ አለ​ቆች ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ነገ​ሥ​ታቱ በክ​ፋ​ታ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቹም በሐ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ተሰኙ።


ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች፤ ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤


ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።