ሆሴዕ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቤ ልቡናቸው ዝሙትን፥ መጠጥንና ስካርን ወደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአመንዝራነት፣ ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤ በእነዚህም የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዝሙት ተከትለዋልና፤ ወይንና አዲስ ወይን ጠጅ ልብን አጥፍቶአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዝሙት ሥራ፥ የቈየና አዲስ የወይን ጠጅን መከተል የሕዝቤን አእምሮ አጥፍቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግልሙትናና የወይን ጠጅ ስካርም አእምሮን ያጠፋል። |
እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ።
በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።
በበዓል ትንቢት የተናገሩበትን የሰማርያን ነቢያት ኀጢአታቸውን አይቻለሁ፤ ሕዝቤን እስራኤልንም አሳትዋቸው።
ሕዝቤ በዝሙት መንፈስ ስተዋልና ከአምላካቸውም ርቀው አመንዝረዋልና በትርን ይጠይቃሉ፤ በትሩም ይመልስላቸዋል።
ወደ አምላካቸው ይመለሱ ዘንድ ልባቸውን አላቀኑም፤ የዝሙት መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ እግዚአብሔርንም አላወቁትምና።
“እንዳትሞቱ ወደ ምስክሩ ድንኳን ስትገቡ ወይም ወደ መሠዊያው ስትቀርቡ አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን ነገር ሁሉ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።
አቤግያም ወደ ናባል መጣች፤ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፤ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።