Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “እን​ዳ​ት​ሞቱ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ስት​ገቡ ወይም ወደ መሠ​ዊ​ያው ስት​ቀ​ርቡ አን​ተና ልጆ​ችህ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርን ነገር ሁሉ አት​ጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እንዳትሞቱ አንተና ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን በምትገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም በልጅ ልጃችሁ ዘንድ የሚጠበቅ ዘላለማዊ ሥርዐት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ጠጥታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዳትገቡ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ትሞታላችሁ፤ ይህም ሕግ ከእናንተ በኋላ በሚነሣውም ትውልድ ዘንድ ሁሉ ተጠብቆ መኖር አለበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን ነገር ሁሉ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 10:9
17 Referencias Cruzadas  

በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


ለተሳዳቢና ለሰካራም ወይን ክፉ ነው፥ ጽዋውንም መላልሶ የሚጨልጥ ጠቢብ አይደለም፥ እንደዚህ ያለ አላዋቂም ሁሉ አንድ ይሆናል።


እነ​ዚ​ህም ደግሞ ከወ​ይን ጠጅ የተ​ነሣ ይስ​ታሉ፤ ከሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ የተ​ነሣ አላ​ዋ​ቆች ይሆ​ናሉ፤ ካህ​ኑና ነቢዩ ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ የተ​ነሣ ይስ​ታሉ፤ በወ​ይን ጠጅም ይዋ​ጣሉ፤ ከሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ የተ​ነሣ ይበ​ድ​ላሉ፤ ይህም የዐ​ይን ምት​ሐት ነው፤ በፍ​ርድ ይሰ​ና​ከ​ላሉ።


ካህ​ና​ቱም ሁሉ በው​ስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ሲገቡ የወ​ይን ጠጅ አይ​ጠጡ።


የሕ​ዝቤ ልቡ​ና​ቸው ዝሙ​ትን፥ መጠ​ጥ​ንና ስካ​ርን ወደደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


ካህ​ኑም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ቍር​ባን አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባል፤ ይህም የቍ​ር​ባን ፍር​ም​ባና የመ​ባው ወርች ለካ​ህኑ የተ​ቀ​ደሰ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ባለ​ስ​እ​ለቱ ወይን ይጠ​ጣል።


ከወ​ይን ጠጅና ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ ራሱን የተ​ለየ ያድ​ርግ፤ ከወ​ይን ወይም ከሌላ ከሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር የሚ​ገ​ኘ​ውን ሆም​ጣጤ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም ጭማቂ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም እሸት ወይም ዘቢብ አይ​ብላ።


እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታላቅ ይሆ​ና​ልና የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ ሁሉ አይ​ጠ​ጣም፤ ከእ​ናቱ ማሕ​ፀን ጀም​ሮም መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​በ​ታል።


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።


የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥


እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለነውረኛ ረብ የማይስገበገቡ፥


ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውሃ ብቻ አትጠጣ።


ኤጲስቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos