የእግዚአብሔርም ብርሃን በጥዋት፥ በማለዳም ፀሐይ ይወጣል፤ ብርሃኑም በነግህ ይመጣል፤ ከዝናምም የተነሣ በምድር ሐመልማል ይለመልማል።
ሆሴዕ 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ሀገራቸውን አድናለሁ፤ በእውነትም እወድዳቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ ውብ አበባ ያብባል፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም፣ ሥር ይሰድዳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ከዳተኝነታቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእስራኤል ሕዝብ እንደሚወርድ ጠል እሆናለሁ። እነርሱ እንደ አበባ ይፈካሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥር ይሰዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ፥ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሩን ይሰድዳል። |
የእግዚአብሔርም ብርሃን በጥዋት፥ በማለዳም ፀሐይ ይወጣል፤ ብርሃኑም በነግህ ይመጣል፤ ከዝናምም የተነሣ በምድር ሐመልማል ይለመልማል።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
ሙታን ይነሣሉ፤ በመቃብር ያሉም ይድናሉ። በምድርም የሚኖሩ ደስ ይላቸዋል፤ ከአንተ የሚገኝ ጠል መድኀኒታቸው ነውና፤ የኃጥኣንንም ምድር ታጠፋለህ።
የዮርዳኖስም ምድረ በዳ ያብባል፤ ሐሤትንም ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብርና የቀርሜሎስ ክብር ይሰጠዋል፤ ሕዝቤም የጌታን ክብር፥ የአምላክንም ግርማ ያያሉ።
በደረቅ መሬት ላይ ለሚሄድና ለተጠማ ውኃን እሰጣለሁ፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፥ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አኖራለሁ፤
“ሰማይ በላይ ደስ ይበለው፤ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ፤ ምድርም መድኀኒትን ታብቅል፤ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክ ፈጥሬሃለሁ።
“ከዳተኞች ልጆች ሆይ! ተመለሱ፤ ቍስላችሁንም እፈውሳለሁ። እነሆ እኛ አገልጋዮችህ እንሆናለን፤ አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና።
ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ይቅር እላቸዋለሁ፤ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
እነሆ፥ አበባዎችን እንደሚያድጉ ተመልከቱ፤ አይፈትሉም፤ አይደክሙም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በክብሩ ዘመን ሁሉ ከእነርሱ እንደ አንዱ አልለበሰም።
ትምህርቴንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድርገው፤ ነገሬ እንደ ጠል ይውረድ፤ በእርሻም ላይ እንደ ዝናም፥ በሣርም ላይ እንደ ጤዛ።