የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
ዕብራውያን 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ልጁ ግን፥ “ጌታ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው፤ የመንግሥትህ በትርም የጽድቅ በትር ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤ “አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ልጁ ግን፥ “አምላክ ሆይ! ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የጽድቅ በትር የመንግሥትህ በትር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ልጁ ግን፥ “አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይኖራል፤ መንግሥትህንም በትክክል ታስተዳድራለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይላል፤ ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። |
የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ነገር ግን የይሁዳን ልጆች ይቅር እላቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸውም እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት ወይም በሰይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠረገላ፥ ወይም በፈረሶች፥ ወይም በፈረሰኞች የማድናቸው አይደለም” አለው።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
አይሁድም፥ “አንተ፥ ሰው ስትሆን ራስህን እግዚአብሔርን ታደርጋለህና፤ ስለ መሳደብህ ነው እንጂ ስለ መልካም ሥራህስ አንወግርህም” አሉት።
እነርሱም አባቶቻችን ናቸው፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ ተወለደ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ ነው፤ አሜን።
ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም።
ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፤ ከሴቶችህ መካን አትኖርም፤ ልጆች የሌሏት አገልጋይም አትኖርም፤ ከከብትህም መካን አይኖርም።
እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።