ዕንባቆም 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፣ ቀስትህንም ገተርህ፣ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስትህን አዘጋጀህ፤ ፍላጻም እንዲመጣልህ አዘዝህ፤ ሴላ ምድርን በወንዞች ከፈልህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስትህን ገለጥህ በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፤ ቀስትህንም ገተርህ፤ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስትህን ከሰገባው አወጣህ፤ ፍላጻህንም ለመወርወር አነጣጠርህ፤ ምድሪቱንም ሰንጥቀህ ወንዞች አስገኘህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፥ ቀስትህንም ገተርህ፥ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ። |
እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፤ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል” አለው። ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት እንዲሁ አደረገ።
እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ተቃዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላጋራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ለዐይኑ የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፤ መዓቱንም እንደ እሳት አፈሰሰ።
ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይኸውም በኋላቸው ከሚሄደው ከመንፈሳዊ ዐለት የጠጡት ነው፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።