ራሔልም፥ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገኝ፤ ብርቱ ትግልንም ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፤ አሸነፍሁም፤ እኅቴንም መሰልኋት” አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።
ዘፍጥረት 49:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ንፍታሌም በፍሬው ላይ ውበትን የሚሰጥ ሰፊ ዘንባባ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ንፍታሌም ነጻ እንደ ተለቀቀች፣ የሚያማምሩም ግልገሎች እንደምትወልድ ሚዳቋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው፥ መልካም ቃልን ይሰጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ንፍታሌም በነጻነት እየተዘዋወረች እንደምትኖር፥ ደስ የሚያሰኙ ግልገሎችን እንደምትወልድ ሚዳቋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው፤ መልካም ቃልን ይሰጣል። |
ራሔልም፥ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገኝ፤ ብርቱ ትግልንም ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፤ አሸነፍሁም፤ እኅቴንም መሰልኋት” አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።
እነርሱም፥ “በዚች ዕለት ለዚህ ሕዝብ ቸርነት ብታደርግላቸው፥ ደስም ብታሰኛቸው፥ መልካም ነገርንም ብትናገራቸው፥ ሁልጊዜ አገልጋዮች ይሆኑልሃል” ብለው ተናገሩት።
በዋሊያና በውርንጭላ ፍቅር፥ ከሚስትህ ጋር ተፋቀር፥ የፍቅርዋ ሞገስ ያርካህ፥ ለአንተ ትሁንህ፥ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ትኑር፤ በዚች ፍቅር ስትፋቀር ብዙ ትሆናለህ።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ወድዶ እስኪነሣ ድረስ፥ ፍቅሬን እንዳትቀሰቅሱትና እንዳታስነሡት፥ በምድረ በዳው ኀይልና ጽናት አምላችኋለሁ።
ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም ከበጎ ነገር ጠግቦአል፤ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕርንና ሊባን ይወርሳል።
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤