ዘፍጥረት 47:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አንተ አዳንኸን፤ በጌታችንም ፊት ሞገስን አገኘን፤ ለፈርዖንም አገልጋዮች እንሆናለን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “እንግዲህ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታችን ፊት ሞገስ ካገኘን፣ ለፈርዖን ገባሮች እንሆናለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “አንተ ሕይወታችንን አተረፍክ፥ ጌታችንን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ፥ ለፈርዖንም ባርያዎች እንሆናለን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም “ጌታችን ሆይ፥ ሕይወታችንን ስላዳንክልንና መልካም ነገር ስላደረግህልን ሁላችንም የፈርዖን ባሪያዎች እንሆናለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አንተ አዳንኸን በጌታችን ፊት ሞገስን አናግኝ ለፈርዖንም ባሪያዎች እንሆናለን አሉት። |
የላካቸው መልእክተኞችም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”
ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን?” አለ። እርሱም፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘቴ ይበቃኛል” አለ።
ፈርዖንም የዮሴፍን ስም “እስፍንቶፎኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ የምትሆን አስኔትንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።
በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፤ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባችሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”
ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዖን እንዲሆን በግብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደረጋት።
እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
ከእንስሳ ሁሉ፥ ከተንቀሳቃሽ አራዊትም ሁሉ፥ ሥጋ ካለው ሁሉ ከአንተ ጋር ትመግባቸው ዘንድ ከሁሉም ሁለት ሁለት ወደ መርከብ ታገባለህ፤ ተባትና እንስት ይሁን።
እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።