ዘፍጥረት 47:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው፤ ከፈርዖንም ፊት ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንን ባርኮም ያዕቆብ ከፈርዖንም ፊት ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ፈርዖንን ባረከውና ተሰናብቶት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው ከፈርዖንም ፊት ወጣ። |
ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ፤ ፈርዖን እንዳዘዘላቸውም በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ርስትን ሰጣቸው።
ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ንጉሡም ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ንጉሡም ቤርዜሊን አቅፎ ሳመው፤ መረቀውም፤ ወደ ስፍራውም ተመለሰ።
ታይም የአድርአዛር ጠላት ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ስለ ተዋጋውና ስለ ገደለው፥ ታይ ልጁን ኢያዱራን ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ፥ ይመርቀውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብርና የወርቅ የናስም ዕቃ ይዞ መጣ፤
እነሆም፥ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን አላቸው። እነርሱም፦ እግዚአብሔር ይባርክህ ብለው መለሱለት።