ዘፍጥረት 46:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንፍታሌምም ልጆች፤ አሴሔል፥ ጎሂን፥ ዮሴር ሴሌም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዬጽርና ሺሌም ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጼርና ሺሌም ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጼርና ሺሌም ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል ጊኑ ዮጽር፥ ሺሌም። |
ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት፤ ባላ የወለደቻቸው ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው።
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም ከበጎ ነገር ጠግቦአል፤ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕርንና ሊባን ይወርሳል።