La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 46:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የያ​ዕ​ቆብ ሚስት የራ​ሔል ልጆች ዮሴ​ፍና ብን​ያም ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ዮሴፍና ብንያም ናቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ዮሴፍና ብንያም ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች ዮሴፍና ብንያም ናቸው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 46:19
18 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ወደ​ዳት፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ስለ ታና​ሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ። ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው።


ስሙ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁለ​ተኛ ወንድ ልጅን ይጨ​ም​ር​ልኝ” ስትል ዮሴፍ ብላ ጠራ​ችው።


የራ​ሔል ልጆች፤ ዮሴፍ፥ ብን​ያም፤


ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ የመ​ጋ​ቢ​ዎ​ቹም አለቃ የሚ​ሆን የግ​ብፅ ሰው ጲጥ​ፋራ ወደ ግብፅ ከአ​ወ​ረ​ዱት ከይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እጅ ገዛው።


አገ​ል​ጋ​ይህ አባ​ታ​ች​ንም እን​ዲህ አለን፦ ሚስቴ ሁለት ወን​ዶች ልጆ​ችን እንደ ወለ​ደ​ች​ልኝ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤


ላባ ለልጁ ለልያ የሰ​ጣት የዘ​ለፋ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ እር​ስ​ዋም እነ​ዚ​ህን ዐሥራ ስድ​ስ​ቱን ነፍስ ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደች።


ለዮ​ሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ናቸው። ሶር​ያ​ዊት ዕቅ​ብቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የም​ና​ሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ የም​ና​ሴም ወን​ድም የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሱታ​ላና ጠኀን ናቸው። የሱ​ታላ ልጅም ኤዴን ነው።


ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብን​ያም፥ ንፍ​ታ​ሌም፥ ጋድ፥ አሴር።


ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፥ ብን​ያም።


ዮሴ​ፍም አስ​ቀ​ድሞ በግ​ብፅ ነበረ። ከያ​ዕ​ቆብ ጕል​በት የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ ነፍ​ሶች ነበሩ፤