Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 29:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ወደ​ዳት፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ስለ ታና​ሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ። ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ያዕቆብም ራሔልን ስለ ወደዳት፣ “ታናሺቱ ልጅህን ራሔልን የምትድርልኝ ከሆነ ሰባት ዓመት አገለግላለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ያዕቆብም ራሔልን ወደደ፥ እንዲህም አለ፦ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ያዕቆብ ራሔልን እጅግ ስለ ወደዳት “ራሔልን ብትድርልኝ ሰባት ዓመት አገለግልሃለሁ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ያዕቆብም ራሔልን ወደደ እንዲህም አለ፦ ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባር ዓመት እገዛልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 29:18
11 Referencias Cruzadas  

በገ​ለ​ዓድ ባይ​ሆ​ንም እንኳ በጌ​ል​ጌላ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ሠዉ አለ​ቆች ስተ​ዋል፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድ​ን​ጋይ ክምር ነው።


ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በም​ት​ጠ​ይ​ቁ​ኝም መጠን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይህ​ችን ብላ​ቴና ግን ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ስጡኝ።”


እኔም በዐ​ሥራ አም​ስት ብርና በአ​ንድ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ተኩል ገብ​ስና በአ​ንድ ፊቀን ወይን ተወ​ዳ​ጀ​ኋት።


ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ፥ “በመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት ያጨ​ኋ​ትን ሚስ​ቴን ሜል​ኮ​ልን መል​ስ​ልኝ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


ለአ​ንተ ቤት የተ​ገ​ዛ​ሁ​ልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆ​ችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎ​ችህ ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለዋ​ወ​ጥ​ኸው።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔ​ል​ንም ከልያ ይልቅ ወደ​ዳት፤ ሌላ ሰባት ዓመ​ትም ተገ​ዛ​ለት።


ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።


ይስ​ሐ​ቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብ​ቃ​ንም ወሰ​ዳት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወደ​ዳት፤ ይስ​ሐ​ቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽ​ናና።


ላባም፥ “ለሌላ ሰው ከም​ሰ​ጣት ይልቅ ለማ​ው​ቅህ ለዘ​መዴ ለአ​ንተ ብሰ​ጣት ይሻ​ላል፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው።


ስለ እነ​ርሱ የተ​ገ​ዛ​ሁ​ላ​ቸ​ውን ሚስ​ቶ​ቼ​ንና ልጆ​ችን ስጠ​ኝና ልሂድ፤ የተ​ገ​ዛ​ሁ​ል​ህን መገ​ዛት ታው​ቃ​ለ​ህና።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios