ያዕቆብም አለ፥ “አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፤ ገንዘብህም በእኔ ዘንድ ካለ በወንድሞቻችን ፊት እይ፤ ለአንተም ውሰደው” አለ። ያዕቆብ ሚስቱ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበርና።
ዘፍጥረት 44:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ከባሪያዎችህ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ይሙት፤ እኛም ደግሞ ለጌታችን አገልጋዮች እንሁን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠፋው ዕቃ ከአገልጋዮችህ የተገኘበት ይሙት፤ የቀረነው የጌታችን ባሮች እንሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠፋው ዕቃ ከአገልጋዮችህ የተገኘበት ይሙት፤ የቀረነው የጌታችን ባሮች እንሁን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኛ አንዱ ይህን ዕቃ ይዞ ቢገኝ በሞት ይቀጣ፤ የቀረነውም የአንተ ባሪያዎች እንሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባሪያዎችህ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ይሙት እኛም ደግሞ ለጌታችን ባሪያዎች እንሁን። |
ያዕቆብም አለ፥ “አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፤ ገንዘብህም በእኔ ዘንድ ካለ በወንድሞቻችን ፊት እይ፤ ለአንተም ውሰደው” አለ። ያዕቆብ ሚስቱ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበርና።
እነዚያም ሰዎች ወደ ዮሴፍ ቤት እንደ ገቡ በአዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፥ “በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኰሉብን፥ ሊወድቁብንም፥ እኛንም በባርነት ሊገዙን፥ አህዮቻችንንም ሊወስዱ ወደዚህ አስገቡን።”
እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
ይሁዳም አለ፦ “ለጌታችን ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የአገልጋዮችህን ኀጢአት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእርሱ ዘንድ የተገኘበትም ደግሞ ለጌታችን አገልጋዮቹ ነን።”
ከበደልሁ ወይም ለሞት የሚያበቃኝ የሠራሁት ክፉ ሥራ ካለ ሞት አይፈረድብኝ አልልም፤ ነገር ግን እነዚህ በደል የሌለብኝን በከንቱ የሚከስሱኝ ከሆነ፥ ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ ለማን ይቻለዋል? እኔ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብያለሁ።”