ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ።
ዘፍጥረት 44:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በታናሹም ዓይበት አፍ የብሩን ጽዋዬንና የእህሉን ዋጋ ጨምረው።” እርሱም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋራ ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋር ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔን የብር ዋንጫ ውሰድና በታናሽ ወንድማቸው ስልቻ ውስጥ እህል ለመሸመት ከመጣው ገንዘብ ጋር ክተተው።” የቤቱም አዛዥ ዮሴፍ እንደ ነገረው አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታናሹም ዓይበት አፍ የብሩን ጽዋዬና የእህሉን ዋጋ ጨምራው። |
ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ።
ዮሴፍም ዓይበታቸውን እህል ይሞሉት ዘንድ አዘዘ፤ የየራሳቸውንም ብር በየዓይበታቸው ይመልሱት ዘንድ፥ ደግሞም የመንገድ ስንቅ ይሰጡአቸው ዘንድ አዘዘ። እንዲህም አደረጉ።
ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ፤ ለእነርሱም ለብቻቸው፤ ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው፤ የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይችሉምና፥ ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።
ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “የእነዚህ ሰዎች ዓይበቶቻቸው መያዝ የሚችሉትን ያህል እህል ሙላላቸው፤ የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤
በግድ የምላችሁ አይደለም፤ ነገር ግን ከእናንተ ለዚህ ሥራ የሚተጉለት አሉና የፍቅራችሁን እውነተኛነት አሁን መርምሬ ተረዳሁ።
አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆን ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስሙ።
በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግልህ ዘንድ ሊፈትንህ፥ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ የመገበህን አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ፥
አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።