Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 44:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋር ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋራ ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የእኔን የብር ዋንጫ ውሰድና በታናሽ ወንድማቸው ስልቻ ውስጥ እህል ለመሸመት ከመጣው ገንዘብ ጋር ክተተው።” የቤቱም አዛዥ ዮሴፍ እንደ ነገረው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በታ​ና​ሹም ዓይ​በት አፍ የብ​ሩን ጽዋ​ዬ​ንና የእ​ህ​ሉን ዋጋ ጨም​ረው።” እር​ሱም ዮሴፍ እን​ዳ​ለው አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በታናሹም ዓይበት አፍ የብሩን ጽዋዬና የእህሉን ዋጋ ጨምራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 44:2
12 Referencias Cruzadas  

ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።


በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ዮሴፍ ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥


ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።


ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው።


ከዚያም አዛዡ ፍተሻውን ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ቀጠለ። በመጨረሻም፥ ጽዋው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ።


ጎሕ ሲቀድ ሰዎቹ ከነአህዮቻቸው ተሸኙ።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ይህንን የምለው ትእዛዝ እንደምሰጥ ሆኜ አይደለም፤ ነገር ግን ሌሎች ከሚያሳዩት ትጋት አንጻር የፍቅራችሁን እውነተኛነት ለመመርመር ነው።


አምላካችሁን ጌታ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ ጌታ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም አላሚውን አትስሙ።


በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ፥ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን፥


ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos