ዘፍጥረት 44:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “የእነዚህ ሰዎች ዓይበቶቻቸው መያዝ የሚችሉትን ያህል እህል ሙላላቸው፤ የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል፣ እንዲሁም ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ “ለመጫን የሚችሉትን ያኽል በየስልቻዎቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ ዓይበታቸው የሚያነሣውን ያህል እህል ሙላላቸው የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤ |
ዮሴፍም ዓይበታቸውን እህል ይሞሉት ዘንድ አዘዘ፤ የየራሳቸውንም ብር በየዓይበታቸው ይመልሱት ዘንድ፥ ደግሞም የመንገድ ስንቅ ይሰጡአቸው ዘንድ አዘዘ። እንዲህም አደረጉ።
እንዲህም ሆነ፤ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በዓይበታቸው ተቋጥሮ አገኙት፤ እነርሱም አባታቸውም የተቋጠረ ብራቸውን አይተው ፈሩ።
ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር በአየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፤ እርድም እረድ፤ አዘጋጅም፤ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።”
ከግብፅም ያመጡትን እህል በልተው ከፈጸሙ በኋላ አባታቸው፥ “እንደገና ሂዱ፤ ጥቂት እህል ሸምታችሁ አምጡልን” አላቸው።
እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ኀይለኛውን ወንድና ኀይለኛዋን ሴት፥ የእንጃራን ኀይል ሁሉ፥ የውኃውንም ኀይል ሁሉ ያስወግዳል፤