Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 44:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ “ለመጫን የሚችሉትን ያኽል በየስልቻዎቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል፣ እንዲሁም ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዮሴ​ፍም የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “የእ​ነ​ዚህ ሰዎች ዓይ​በ​ቶ​ቻ​ቸው መያዝ የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል እህል ሙላ​ላ​ቸው፤ የሁ​ሉ​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው አፍ ጨም​ረው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ ዓይበታቸው የሚያነሣውን ያህል እህል ሙላላቸው የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 44:1
8 Referencias Cruzadas  

አብርሃም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ በመሆን ለረዥም ዘመን የኖረውን አገልጋዩን እንዲህ አለው፤ “እጅህን በጒልበቴ ላይ አድርገህ ማልልኝ፤


ዮሴፍ አገልጋዮቹን “ለእነዚህ ሰዎች በየስልቻዎቻቸው እህል ሙሉላቸው፤ ገንዘባቸውንም መልሳችሁ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ቋጥሩላቸው፤ ለጒዞአቸውም ስንቅ አስይዙአቸው” ብሎ አዘዘ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥


ከዚህ በኋላ እህላቸውን ከስልቾቻቸው ባራገፉ ጊዜ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ገንዘባቸውን እንደ ተቋጠረ አገኙ፤ እነርሱና አባታቸው የተመለሰውን ገንዘብ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ።


ዮሴፍ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ ጠራውና “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ ዛሬ ቀን ከእኔ ጋር ምሳ ስለሚበሉ አንድ ከብት ዕረድና አዘጋጅ” አለው።


ስለዚህ ወደ ቤቱ በር አጠገብ ሲደርሱ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አሉት፤


የያዕቆብ ቤተሰብ ከግብጽ የመጣውን እህል ተመግበው በጨረሱ ጊዜ አባታቸው “እንደገና ወደ ግብጽ ሂዱና ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው።


የእኔን የብር ዋንጫ ውሰድና በታናሽ ወንድማቸው ስልቻ ውስጥ እህል ለመሸመት ከመጣው ገንዘብ ጋር ክተተው።” የቤቱም አዛዥ ዮሴፍ እንደ ነገረው አደረገ።


እነሆ ጌታ የሠራዊት አምላክ፥ ሕዝቡ ኀይልና ብርታት አግኝተው የሚኖሩበትን ምግብና ውሃ፥ ሌላም ነገር ሁሉ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ያስወግዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos