ዘፍጥረት 40:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛውም ቀን የፈርዖን የልደት በዓል ነበረ፤ ለሹማምቱም ሁሉ ግብር አበላ። በዚያ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምቱ ባሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስተኛውም ቀን የፈርዖን የልደት በዓል ነበረ፤ ለሹማምንቱም ሁሉ ግብር አበላ። በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምንቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለ ነበረ ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ቀን የወይን ጠጅ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኀላፊው ከእስር ቤት ወጥተው በመኳንንቱ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሦስተኛውም ቀን ፈርዖን የተወለደበት ቀን ነበረ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ከፍ አደረገ። |
እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈርዖን ሹመትህን ያስባል፤ ወደ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃነትህም ይመልስሃል፤ ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታደርገው እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሹመትህም የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ይቈርጥሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ የሰማይ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”
ሰሎሞንም ነቃ፤ እነሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ በጽዮንም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ፤ የደኅንነትንም መሥዋዕት አቀረበ፤ ለአገልጋዮቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ።
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ከፍ አደረገው፤ ከወህኒ ቤትም አወጣው፤
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፥ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የኢኮንያንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ፤ ከወህኒም አወጣው፤