ዘፍጥረት 38:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ የበኵር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ ጌታም ቀሠፈው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበረ፥ እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔር ቀሠፈው። |
እኛ ይህችን ስፍራ እናጠፋታለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋትም ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል።”
የይሁዳም ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስሮም፥ ይሞሔል፤
ኤልያስም፥ “እኔ በቤቷ ያደርሁ የዚች መበለት ምስክርዋ ጌታዬ ሆይ፥ ልጅዋን በመግደልህ ክፉ አድርገህባታልና ወዮልኝ!” ብሎ ጮኸ።
የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ሴት ከሴዋ ልጅ ተወለዱለት። የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደለውም።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ። መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገርን አደረገ።
ሰውስ ሰውን ቢበድል ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩለታል፤ ሰው ግን እግዚአብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸልዩለታል?” እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወድዶአልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።